አፕወርክ ( #upwork )
በዓለም ላይ ከሚገኙ ትላልቅ የፍሪላንስ (Freelance) ሥራ ማገናኛ ፕላትፎርሞች ግንባር ቀደሙ ነው። ሥራ የሚያሠሩ አካላትን (ኩባንያዎችን፣ የንግድ ድርጅት ባለቤቶችን ወይም ግለሰቦችን) እና በግል (ብዙውን ጊዜ በርቀት) ሥራ መስራት የሚፈልጉ የሙያ ባለቤቶች (Freelancers) የሚያገናኝ ዲጂታል የገበያ ቦታ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን ይሄን ድረ ገጽ በመጠቀም ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ፤ በርካቶች ደግሞ ባለማወቅና አጠቃቀሙን ባለመረዳት እድሉ ያመልጣቸዋል። በመሆኑም አንዳአንዶች በተደጋጋሚ ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት ደረጃ በደረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።
--- --- ---
በአፕወርክ ላይ የሚሰሩ ክፍያዎች በተለምዶ በሁለት መንገድ ይፈጸማሉ፡
1. በተወሰነ ዋጋ (Fixed-Price Contracts)፦ የተወሰነ የሥራ ደረጃ ወይም ሙሉውን ፕሮጀክት አጠናቅቀው ሲያስረክቡ አስቀድሞ የተስማሙበትን ክፍያ ያገኛሉ።
2. በሰዓት (Hourly Contracts)፦ ለሠሩበት እያንዳንዱ ሰዓት ክፍያ የሚፈጸምበት ነው። ይህም ብዙውን ጊዜ በአፕወርክ የኮምፒውተር መተግበሪያ (Desktop App) አማካኝነት ይቆጠራል።
---
አፕወርክ ላይ ሥራ እንዴት መጀመር ይቻላል❓
#ደረጃ 1. መለያ መክፈት እና መመዝገብ
👉 ወደ አፕወርክ ድረ ገጽ በመሄድ "Sign Up" የሚለውን መጫን፤
👉 በመቀጠል "I'm a freelancer, looking for work" የሚለውን መምረጥ፤ 👉 በስራ ኢሜይል፣ በGoogle ወይም በApple ID መመዝገብ ይቻላል።
#ደረጃ 2. ማራኪ ፕሮፋይል መገንባት:- ፕሮፋይል እንደ ሲቪ እና ማስተዋወቂያ ገጽ ሆኖ ያገለግላል።
ይህም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ማካተት ይኖርበታል።
👉 ሙያዊ ፎቶ - ግልጽ፣ ፈገግታ ያለው እና ሙያዊ የሆነ የፊት ፎቶ ይጠቀሙ።
2. ግልጽ የሥራ መደብ ርዕስ:- እንደ "Freelancer" የመሳሰሉ አጠቃላይ/General ቃላትን / ርዕሶችን አትጠቀሙ፤ ይልቁንም ትክክለኛ እና ሙያችሁን የሚገልጹ ቃላትን ተጠቀሙ (ምሳሌ፦ Slack Developer፣ E-commerce Expert ወይም SEO Content Writer . . .)
3. የአገልግሎት ማጠቃለያ፦ ትኩረታችሁ ለደንበኛው ምን ዓይነት መፍትሔ መስጠት እንደሚችል ላይ አድርጉ። ደንበኞች ሙሉውን ከፊታቸው ከፍተው የማንበብ ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት የመጀመሪያዎቹን ሁለት መስመሮች ስለሚያዩ፣ እነዚያን መስመሮች ማራኪ አድርጓቸው።
4. የሥራ ናሙናዎች (Portfolio)፦ ቀደም ሲል የሠችኋቸው ሥራዎች፣ ፕሮጀክቶች ወይም የሥራ ናሙናዎች አያይዙ (Upload አድርጉ)። የሥራ ናሙና ያላቸው ፕሮፋይሎች የደንበኞችን ትኩረት የማግኘት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
5. የክፍያ ተመን እና ክህሎቶች፦ ተወዳዳሪ የሆነ መነሻ ክፍያ ተመን አዘጋጁ፤ ከሙያችሁ ጋር የሚሄዱ እስከ 15 የሚደርሱ የክህሎት መለያዎችን (Skill tags) ምረጡ።
#ደረጃ 3. "Connects" ምን እንደሆነ መረዳት
አፕወርክ ለስራ ለማመልከት #Connects የተባሉ ዲጂታል ቶከኖችን (Virtual tokens) ይጠቀማል።
🙏 አዲስ መለያ ስትከፍቱ የተወሰኑ Connects በነጻ ይሰጣችኋል።
🙏 እንደ ሥራው ዓይነት እና መጠን ለሥራ ለማመልከት (Proposal ለማስገባት) ከ2 እስከ 16 Connects ሊጠይቃችሁ ይችላል።
🙏 ለቃለ-መጠይቅ ከተመረጣችሁ ተጨማሪ ነፃ Connects ታገኛላችሁ፤ በቂ ካልሆነ በቀጥታ ገዝታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
#ደረጃ 4. ትክክለኛ ስራ ፈልጉ
የፍለጋ ማጣሪያዎች (Filters) በመጠቀም የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ ሥራዎችን ለዩ።
👉 የደንበኛው ታሪክ፦ ደንበኛው Payment Verified (የክፍያ መረጃው የተረጋገጠ) የሚል ምልክት ያለው እና ጥሩ ግምገማዎች/ደረጃዎች (Ratings) ያሉት መሆኑን አረጋግጡ።
👉 የልምድ ደረጃ፦ የሙያው አዲስ ጀማሪ ከሆናችሁ ከልምዳችሁ ጋር የሚጣጣም Entry Level ወይም Intermediate ፕሮጀክቶችን ለማግኘት ማጣሪያው ተጠቀሙ።
#ደረጃ 5. ጠንካራ ማመልከቻ (Proposal) አስገቡ
👉 ለሥራ በምታመለክቱበት ጊዜ የማመልከቻ ደብዳቤ (Cover Letter) መጻፍ ይኖርባቸዋል (Ai መጠቀም እና ራሳችሁ አርትኦት መስራት ትችላላችሁ)
👉 የደንበኛውን ስም በግምገማዎች (Reviews) ላይ ካገኛችሁ በስሙ ጠርታችሁ ሰላም በሉት።
👉 በመጀመሪያዎቹ 2–3 ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ በቀጥታ የደንበኛውን ችግር ወይም ፍላጎት እንዴት መፍታት እንደምትችሉ አብራሩ።
👉 ከሥራው ጋር በጣም ተዛማጅ የሆኑ 1–2 የሥራ ናሙናዎችን አያይዘው ይላኩ።
#ደረጃ 6. ሥራውን አጠናቅቃችሁ ክፍያችሁን ተቀበሉ
👉 ከተቀጠራችሁ በኋላ በአፕወርክ የመልእክት መለዋወጫ (Upwork Messages) በኩል የቅርብ ግንኙነት አድርጉ/ተጻጻፉ።
👉 በተወሰነ ዋጋ (Fixed-Price) ለሚሠሩ ፕሮጀክቶች፣ ሥራ ከመጀመራችሁ በፊት ደንበኛው የሥራውን ደረጃ ክፍያ (Milestone) ማስያዙን አረጋግጡ።
👉 በሰዓት (Hourly) ለሚሠሩ ፕሮጀክቶች፣ የሠራችሁበትን ሰዓት ለመመዝገብ የUpwork Work Diary መተግበሪያ ተጠቀሙ።
👉 ሥራው ተጠናቅቆ ሲጠናቀቅ ክፍያው በቀጥታ ወደተያያዘው የባንክ ሂሳባችሁ፣ PayPal ወይም Payoneer ወይም ሌላ አማራጭ ገቢ ይሆናል።
💡 ለአዲስ ጀምሪዎች ጠቃሚ ምክሮች
👉 የተዘጋጁ ማመልከቻዎችን በጅምላ አይላኩ (Don't Copy-Paste)፦ አንድ ዓይነት ማመልከቻ ለሁሉም ሰው መላክ Connects በከንቱ ያባክናል።
🙏 የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ለደንበኛው ችግር ተስማሚ አድርጎ ማዘጋጀት የደንበኞችን ምላሽ የማግኘት ዕድልን ያሰፋል።
👉 ሁሉም ሥራዎች እና ክፍያዎች በአፕወርክ ላይ ብቻ አድርጉ፦ ውል ከመፈረማችሁ በፊት ከአፕወርክ ውጭ በሚገኙ መተግበሪያዎች (ለምሳሌ WhatsApp, Telegram) መነጋገር ወይም ከወኪሉ ውጭ ክፍያ መቀበል ፈጽሞ አይፈቀድም። ይህ የአፕወርክን ሕግ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ የክፍያ ዋስትናዎን (Upwork Payment Protection) ያሳጣል።
👉 በጥሩ አስተያየቶች ለመጀመር አነስተኛ ሥራዎችን ስሩ፦ ለመጀመሪያዎቹ 3–5 ሥራዎች ዋና ዓላማችሁ የ 5-ኮከብ ግምገማዎችን (5-star reviews) ማግኘት እንጂ ትልቅ ክፍያ መሰብሰብ መሆን የለበትም። 5-ኮከብ ሌላ ስራ ለማግኘት በእጅጉ ጠቃሚ ነው። በፕሮፋይላችሁ ላይ ጥሩ ስምና ተቀባይነት ለመገንባት አነስተኛ እና ግልጽ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ተቀበሉ።
👉 ግንኙነት አታቋርጡ:- ሥራ መጀመራችሁን ለደንበኛው ማሳወቁን አትርሱ፤ በሥራው ሂደትም መረጃ ስጡ፤ ለምትጠየቁት ፈጥናችሁ መልሱ። ጥሩ ግንኙነት ማድረግ ጥሩ ግምገማዎች/አስተያየቶች ለማግኘት ወሳኝ ነው።
.
.
.
.
.
#የConnects_ዋጋ እና #መግዣ_መንገዶች
1. የConnects ዋጋ
በአፕወርክ (Upwork) ላይ 1 Connect ዋጋው $0.15 ዶላር ነው።
* 10 Connects = $1.50 ዶላር (ከነ ታክስ/VAT ጋር በትንሹ ሊጨምር ይችላል) ማለት ነው።
* አፕወርክ ላይ በትንሹ መግዛት የሚቻለውም የ10 Connects ጥቅል ($1.50) ነው።
---
2. Connects መግዛት የሚቻልባቸው መንገዶች